ሙገር ሲሚንቶ ወጣቶች ላይ አነጣጥሯል
ወጣቶችን ከታች በማሳደግ የሚታወቀው ሙገር ሲሚንቶ አሁንም ከተለያዩ የብሄራዊ ሊግ ክለቦች ወጣቶችን እየመለመለ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ ግርማ ሀብተ ዮሀንስ የአጥቂ መስመሩን እና የአማካዩን ክፍል በማጠናከር ላይም ይገኛሉ፡፡ ከሱሉልታ ከነማ የቀድሞ የአየር ሀይል የመስመር ተጫታዋች የነበረውን አቤል ታሪኩን አስፈርመዋል፡፡
መከላከያአጥቂየማስፈረምጥረቱንአጠናክሯል
መከላከያ ወደ መብራት ሀይል የተጓዘው ማናዬ ፋንቱን ቦታ ለመተካት የመድህኑን መሀመድ ናስር ለማዛወር ከጫፍ ደርሷል፡፡ መሀመድ በቅዱስ ጊዮርጊስም የሚፈለግ ሲሆን የአጥቂው ቀጣይ ማረፊያ ጦሩ ሊሆን ይችላል፡፡ በተያያዘ ዜና ጦሩ የመብራት ሀይሉን በረከት ይሳቅ ለማስፈረም ጥረትሲጀምር የክንፍ ተጫዋች የሆነው ሳሙኤል ታዬ ለ2 ዓመት በክለቡ ለመቆየት ውሉን አድሷል፡፡
ዳሽን ቢራ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል
ዳሽንቢራ በቅርቡ ከሀዋሳ ከነማ የተሰናበተው ቢንያም ሀብታሙ (ኦሼ)ን አስፈርሟል፡፡ ኦሼ ለ2 ዓመት ለመጫወት የፈረመ ሲሆን ፤ የፊርማ ክፍያውም 600 ሺህ ብር ነው፡፡ ቢንያም ዳሽን ቢራን በቅርቡ የለቀቀውን የናይጄሪዊውን ኢማኑኤል ፌቮርን ቦታ የሚተካ ይሆናል፡፡ ፌቮር ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ የነበረ ሲሆን ያቀረበው የ1 ሚሊዮን ብር የፊርማ ክፍያ እና የ1 ሺህ ዶላር ወርሃዊ ደሞዝ ቡና ተጫዋቹን እንዲያስፈርም እንቅፋት ሆኗል፡፡
ፌቮር በሀዋሳ ከነማ እና በቀድሞ ክለቡ መብራት ሀይል ይፈለጋል፡፡ በሌላ የዝውውር ዜና ዳሽን የመከላከያው መድሀኔ ታደሰን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶል ፤ ከባህርዳር ከነማ 3 እንዲሁም 1 ከአማራ ውሃ ስራዎች ተጫዋች አስፈርሞል፡፡ አይናለም ሀይለ እና አስራት መገርሳ ከዳሽን ጋር ለመቆየት ተስማምተዋል፡፡
መድህን ማንጎን ሊቀጥር ይችላል
ኢትዮጵያ መድህን የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና እና የሱሉልታ ከነማ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን በዋና አሰልጣኝነት ሊሾም ይችላል፡፡ አባይነህ ደግሞ ምክትል ሆነው እንደሚሰሩ ተነግሯል፡፡
የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች መታገድ ኢትዮጵያ ቡናን ተጫዋች ከማስፈረም እያገደው ነው
የደጋፊ ማህበሩ አመራሮቹን ያገደው የኢትዮጵያ ቡና ክለብ የደጋፊው ማህበር 2 ምርጥ አጥቂዋችን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶ የነበረ መሆኑ ተነግሯል፡፡