ወደ አልጀርስ የሚያመሩ 18 የሉሲዎቹ ተጫዋቾች ታወቁ

በጋና ለሚስተናግደው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ወደ አልጀርስ በካይሮ ትራንዚት በማድረግ ያመራል፡፡ ሉሲዎቹ ከአልጄሪያ ጋር ላለባቸው የድርሶ መልስ ጨዋታ ላለፈው አንድ ወር ዝግጅታቸውን ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን ዛሬ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ የመጨረሻ 18 ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጋለች፡፡

አሰልጣኝ ሰላም በዝግጅት ላይ ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል አምስቱን ከአልጀርሱ ጨዋታ ውጪ ያደረገች ሲሆን አባይነሽ ኤርቄሎ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ፣ በጉዳት ላይ የምትገኘው መስረም ካንኮ፣ ቤዛዊት ተስፋዬ እና ቤተልሔም ሰማን ወደ አልጄሪያ ከሚጓዘው ቡድን ውስጥ የተቀነሱ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ጨዋታ የፊታችን ረቡዕ በስታደ ጁላይ 5 ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሲደረግ ጨዋታውን የጋምቢያ አርቢትሮች ይመሩታል፡፡

ሙሉ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች (2)

ንግስት መዓዛ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት)

ተከላካዮች (5)

መሠሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው (ኤሌክትሪክ) ፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ገነሜ ወርቁ (ጌዴኦ ዲላ)

አማካዮች (6)

ሠናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አረጋሽ ከልሳ (አካዳሚ) ፣ ዙሌይካ ጁሀድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ አለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች (5)

ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)