ዋልያዎቹ በብራዚል የዝግጅት ጨዋታ ሽንፈት አስተናገዱ

ለ2015 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት በብራዚል የተቀመጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ የዝግጅት ጨዋውን አድርጎ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

በብራዚል የሊግ ተዋረድ የመጨረሻው የሊግ መዋቅር ውስጥ የሚገኘው ኤሲ አናፖሊና ዶ ሬሞን በባኤናዎ ጋማ ስታድየም የገጠመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 1-0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የብራዚሉ ክለብ የድል ግብ የተቆጠረችው ገና በ18ኛው ደቂቃ ሲሆን ግብ አስቆጣሪው አልቪኖ የተባለ ተጫዋች ነው፡፡

ዋልያዎቹ በቪዛ ችግር ምክንያት የቡድኑን ግማሽ ተጫዋቾች ብቻ ይዘው ወደ ብራዚል ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን በጨዋታውም በተጠባባቂ ወንበር ላይ የነበረው ሲሳይ ባንጫ ብቻ ነበር፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ቀጣይ ጨዋታውን በመጪው ቅዳሜ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፎቶ – ሄናልዶ ኦ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *