ሴቶች ዝውውር| ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአምስት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

የአሰልጣኝ ቅጥር በመፈፀም በህዳር ወር ለሚጀመረው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል። 

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿ ዐይዳ ኡስማንን ከአዳማ ከተማ እና ግብ ጠባቂዋ ደስታ ከበደ ከአዲስ አበባ ክለቡን በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀሉ አዲስ ፈራሚዎች ሲሆኑ ብዙሀን እንዳለ፣ ምስጋና አሰፋ፣ መቅደስ ማስረሻ፣ እድላዊት ተመስገን እና አያንቱ ውብዓየሁ ውላቸውን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ያራዘሙ ተጫዋቾች ናቸው። በክለቡ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ያላቸው በመሆኑ በክረምቱ ብዙ ለውጦች ላይኖሩ እንደሚችሉም ተነግሯል።

ድሬዳዋ ከተማ ብዙዓየሁ ጀምበሩን ዋና አሰልጣኝ ፣ ዓለምሰገድ ወልደማርያምን ረዳት አሰልጣኝ አድርጎ በሳምንቱ አጋማሽ መሾሙ የሚታወስ ነው።