ብሄራዊ ቡድኑ በመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታው ሽንፈት አስተናገደ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ባደረገው የመጀመርያ የምድብ ማጣርያ ጨዋታ የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድንን አዲስ አበባ ስታድየም ላይ አስተናግዶ 2-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት የበረሃ ቀበሮዎቹ ሲሆኑ አጥቂው ሶውዳኒ ከግራ መስመር የተሸገረውን ኳስ ተጠቅሞ ግብ አስቆጥሯል፡፡ ከግቧ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች የግብ እድሎችን ፈጥረዋል፡፡

ከእረፍት መልስ በ83ኛው ደቂቃ ብራሂሚ የአልጄርያን መሪነት ወደሁለት ከፍ ያደረገችውን ግብ ሲያስቆጥር በ95ኛው ደቂቃ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አምበሉ ሳላዲን ሰኢድ አስቆጥሮ ጨዋታው በአልጄርያ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው የአልጄርያ የግራ መስመር ለዋልያዎቹ ፈተና የነበረ ሲሆን ለቀኝ መስመር ተከላካዩ አሉላ ግርማ ሽፋን የሚሰጥ ሆልዲንግ ወይም የመስመር አማካይ አለመኖሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ዋጋ አስከፍሎታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጪው ረቡእ ወደ ማላዊ ተጉዞ ሁለተኛ የምድብ ማጣርያውን ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *