ደቡብ ፖሊስ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ የኤርሚያስ በላይን ዝውውር አጠናቆ የግሉ አድርጓል። 

ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን 2006 ላይ የተገኘው የመሀል አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በሀዋሳ ከተማ የዋናው ቡድን ጥቂት ቆይታን ካደረገ በኃላ ወደ አርባምንጭ ከተማ አቅንቶ መጫወት ችሏል። ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ ሰበታ ከተማ ያሳለፈው ተጫዋቹ አዲስ አዳጊው ደቡብ ፖሊስን በአንድ ዓመት የውል ስምምነት ተቀላቅሏል። 

ከግማሽ በላይ ስብስቡን በአዲስ መልክ እያዋቀረ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ 17ኛ ተጫዋቹን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ