የከፍተኛ ሊግ ምድቦች ታውቀዋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖች በየትኞቹ ምድቦች መደልደላቸውን አውቀዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2010 የውድድር ዓመት ግምገማ እና የ2011 ዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ዙሪያ በኢትዮጵያ ሆቴል መካሄድ ቀጥሏል። ውድድሩ በ36 ክለቦች መካከል በሦስት ምድቦች ተከፍሎ መካሄድ እንደሚቀጥል ከሰዓታት በፊት መነገሩ ይታወቃል። አሁን ደግሞ በማዕከላዊ ፣ መካከለኛ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም መካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ በተሰኙት ምድቦች የተደለደሉ ክለቦች ታውቀዋል።
በዚህም መሰረት ዝርዝሩ የሚከተለውን ይመስላል።

ማዕከላዊ ምድብ

ወልዲያ
አውስኮድ
አክሱም ከተማ
ደሴ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ለገጣፎ ከተማ
ቡራዩ ከተማ
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
ገላን ከተማ
ወሎ ኮምቦልቻ
ሰበታ ከተማ
ፌደራል ፖሊስ

መካከለኛ እና ደቡብ ምስራቅ ምድብ

የካ ክፍለ ከተማ
ኢኮስኮ
ዲላ ከተማ
ሀላባ ከተማ
ናሽናል ሲሚንቶ
ወልቂጤ ከተማ
ሀምበሪቾ ዱራሜ
አርሲ ነጌሌ
አዲስ አበባ ከተማ
ኢትዮጵያ መድን
ወላይታ ሶዶ
ድሬዳዋ ፖሊስ

መካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ ምድብ

ነጌሌ ከተማ
ቡታጅራ ከተማ
ጅማ አባ ቡና
ሀዲያ ሆሳዕና
ነቀምት ከተማ
ስልጤ ወራቤ
ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ
ካፋ ቡና
ቤንች ማጂ ቡና
አርባምንጭ ከተማ
ሺንሺቾ ከተማ
ሻሸመኔ ከተማ

ጉባዓው በመቀጠል ወደ ዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት እንደሚሄድ ይጠበቃል።


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ