በግብፅ ሱፐር ካፕ አል አህሊ ከ ዛማሌክ ዛሬ ምሽት ለሚያደርጉት ጨዋታ በመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ የተካተተው ሳላዲን አሲድ ለአል አህሊ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሙገር እና ዋዲ ዴግላ ኮከብ ወደ አፍሪካው ታላቅ ክለብ ከተሸጋገረ ወራት ያስቆጠረ ሲሆን ዛሬ በሚደረገው የግብፅ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋ ላይ በቋሚ አሰላለፍነት ይጀምራል፡፡
የ2013/14 የግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮኖቹ አል-አህሊ ተጋጣሚ የሆኑት የግብፅ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ዛማሌሎች በአንድ ወቅት ሳላዲን ሰኢድን ለመውሰድ ከጫፍ ደርሰው የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ በአፍሪካ ውድድር ለዛማሌክ መጫወት የማይችል በመሆኑ ዝውውሩ መክሸፉ ይታወሳል፡፡
ጨዋታው 2 ሰአት የሚጀምር ሲሆን በአረብ ሳት MBC MASR ላይ መከታተል ይቻላል፡፡
በኦንላይን ስትሪም ለመከታተል ይህንን ሊንክ ይጫኑ —- http://www.m7atat.com/2014/02/mbc-masr-live.html