የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል የሆነው ሳላዲን ሰኢድ በአዲሱ ክለቡ አል-አህሊ የመጀመርያ የነጥብ ጨዋታውን አድርጎ ከቡድኑ ጋር የግብፅ ሱፐር ካፕ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡
ሳላዲን ጨዋታውን በቋሚ ተሰላፊነት የጀመረ ሲሆን የጨዋታውን 2/3ኛ ክፍለ ጊዜ ተጫውቶ በ78ኛው ደቂቃ በቀላል ጉዳት ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡
የጨዋታው መደበኛ 90 ደቂቃ 0-0 በሆነ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት አል-አህሊ 6-5 በሆነ ውጤት አሸነፎ የ2014 የግብፅ ሱፐር ካፕ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡