ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ | የመከላከያ የመጀመርያ 11 ተሰላፊዎች ታውቀዋል 

በቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ የሚወክለው የመከላከያ ቡድን ዛሬ ማምሻውን ናይጄሪያ ላይ ከሬንጀርስ ኢንተርናሽናል ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የመጀመርያ ተሰላፊዎች ታውቀዋል፡፡

ምሽት 12;00 ላይ ጨዋታውን የሚያደርገው  ጦሩ ትላንት ወደ ስፍራው ያቀና ሲሆን አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ለዛሬው ጨዋታ የሚጠቀሙበትን የመጀመርያ አሰላለፍ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። 

አሰላለፉ ይህንን ይመስላል:-

ይድነቃቸው ኪዳኔ 

ሽመልስ ተገኝ (አ) – አበበ ጥላሁን – አዲሱ ተስፋዬ ዓለምነህ ግርማ 

ዳዊት ማሞ – ቴዎድሮስ ታፈሰ – ዳዊት እስጢፋኖስ – ፍሬው ሰለሞን

ተመስገን ገብረኪዳን – ምንይሉ ወንድሙ

ተጠባባቂዎች

አቤል ማሞ፣ ታፈሰ ሰርካ፣ ምንተስኖት ከበደ፣ በኃይሉ ግርማ፣ አማኑኤል ተሾመ፣ ሳሙኤል ታዬ፣ ፍፁም ገብረማርያም

ይህን ጨዋታ የኒጀር ዜግነት ያላቸው ዳኞች ይመሩታል።