​በአምላክ ተሰማ ለቻን 2018 ጨዋታዎች የተመረጡ ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ በቀጣዩ ወር በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2018 የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ላይ እንዲዳኙ በካፍ ከተመረጡ 16 የመሀል ዳኞች መካከል አንዱ ሆኗል።

በአምላክ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሲሆን በ2017 ስኬታማ አመት ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ የፈረንጆች አመትን የቻን ጨዋታዎችን በመምራት የሚያሟሽ ይሆናል። 

በአምላክ በዚህ አመት የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ፣ የአለም ከ17 አመት በታች ዋንጫ ጨዋታዎች እና ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው የአፍሪካ ዞን የአለም ዋንጫ ማጣርያ እና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ከመምራቱ በተጨማሪ በ2018 የሩሲያ አለም ዋንጫ ላይ እንዲዳኙ በእጩነት ከተያዙ 6 የአፍሪካ ዳኞች አንዱ መሆን ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *