ወልዋሎ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታው የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ

በስድስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ቅዳሜ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን ለመግጠም መርሐ ግብር የወጣለት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ እሁድ እንዲሸጋገርለት ጠየቀ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ከመከላከያ ጋር የነበረው ጨዋታ በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ምክንያት ወደ ሰኞ በመሸጋገሩ ቡድኑ ቀጣይ ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ላለበት ጨዋታ በቂ የዝግጅት ግዜ እንደሌለው የገለጸው ክለቡ እሁድ ታኅሳስ 7 የትግራይ ስታድየም ከማንኛውም ፕሮግራም ነፃ በመሆኑ በዚህ ቀን እንዲደረግ አያይዞ ገልፅዋል።