ፋሲል ከነማ ከሐረር ወሳኝ ሦስት ነጥቦች ይዞ ተመልሷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ወደ ሐረር ያመራው ፋሲህ ከነማ ባለሜዳው ድሬዳዋ ከተማነ 1-0 አሸንፎ የዓመቱ ሁለተኛ የሜዳ ውጪ ድል አስመዝግቧል።

ፋሲል ከነማ ጎንደር ላይ ከመከላከያ 2-2 ከተለያየው ስብስብ በዛብህ መለዮን በአብዱረህማን ሙባረክ፣ ከድር ኩሊባሊ እና ጀማል ጣሰው በኤፍሬም ዓለሙ፣ ከድር ኩሊባሊ እና ሚካኤል ሳማኪ ምትክ ወደሜዳ ሲገቡ በድሬድዋ በኩል በዘነበ ከበደ እና ወሰኑ ማዜ ምትክ ኃይሌ እሸቱ እና ምንያህል ይመር በመጀመርያው አሰላለፍ ተካተዋል። በ16ኛው ደቂቃ ሱራፌል ዳኛቸው ከሳጥን ዉጪ አክርሮ በመታት ያስቆጠረው ጎል አጼዎቹን አሸናፊ አድርጓል። 

ጨዋታውን አስመልክቶ የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ዮሀንስ ሳህሌ – ድሬዳዋ ከተማ

“ጨዋታው ጥሩ ነበር። እኛም በእንቅስቃሴ ጥሩ ነበርን። ነገር ግን በቡድኔ ውስጥ እየታየ ያለው ግብ የማግባት ችግር ነው። ይህን ለመቅረፍ እየሰራን እንገኛለን። ዛሬም ያገኘናቸውን ዕድሎች በአግባቡ ብንጠቀም ይህን ውጤት ልናይ አንችልም ነበር። ብንሸነፍም ቡድኔ ጥሩ ነው ።”

ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

“ያደረግነው እንቅስቃሴ የሚገባንን ውጤት ሰቶናል። ከዚህም በተሻለ ግብ ማግባት እንችል ነበር። ከርቀት ተጉዘን እንደመምጣታችን ተጫዋቾቼ ባሳዩኝ ነገር ኮርቻለሁ፡፡”