ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር

ከ9ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነውን የሀዋሳ እና የአባ ጅፋር ጨዋታ በቅድመ ዳሰሳችን ተመልክተነዋል።

ነገ 09፡00 ላይ ሀዋሳ ከተማ በዘጠነኛ የሊግ ጨዋታው ስድስተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉትን አባ ጅፋሮች ያስተናግዳል። ጨዋታው የመጨረሻ የሊግ ጨዋታዎቻቸውን ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ሁለቱ ክለቦች እርስ በርስ የሚያገናኝ ጨዋታም ይሆናል። ስሑል ሽረን በሰፊ የግብ ልዩነት ከረቱ በኋላ ተከታይ በነበረው የሮዱዋ ደርቢ 1-0 የተረቱት ሀዋሳዎች የሊጉን መሪነት ለኢትዮጵያ ቡና ቢያስረክቡም ከመሪው ጋር ያላቸውን የአራት ነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ለመመለስ ከቻምፒዮኖቹ ጋር ይፋለማሉ። ከቻምፒዮንስ ሊጉ መልስ ተስተካካይ ጨዋታዎቻቸውን ከስር ከስር እያከናወኑ የሚገኙት ጅማዎች ደግሞ በተከታታይ ያደረጓቸውን ሁለት ጨዋታዎች ያለግብ አቻ በመለያየት ጨርሰው ነው ሀዋሳን የሚገጥሙት። በመጀመሪያው ሳምንት አዳማን ከረቱበት ጨዋታ በኋላም ዳግም ወደ አሸናፊነት በመመለስ ወደ ፉክክሩ ለመቅረብ ጥረት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል። 

በሦስተኛው ሳምንት በተመለከተው የቀይ ካርድ የመጨረሻ ቅጣቱን በዚህ ጨዋታ የሚጨርሰው የሀዋሳ ከተማው ተከላካይ ያኦ ኦሊቨር የማይሰለፍ ሲሆን አዳነ ግርማ እና ታፈሰ ሰለሞን ወደ ሜዳ እንደሚመለሱ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የጅማ አባ ጅፋሮቹ ዘሪሁን ታደለ እና ዐወት ገብረሚካኤል አሁንም ከጉዳት ያልተመለሱ ሲሄን በሲዳማ ቡናው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የወጣው ተስፋዬ መላኩም በቅጣት ከነገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በጉዳት እና ቅጣት የሳሳው የቡድኑ የቀኝ መስመር ተከላካይ ክፍል ከእረፍት ወደ ቡድኑ በተመለሰው ያሬድ ዘውድነህ እንደሚሸፈን ይጠበቃል። 

የእርስ በርስ ግንኙነቶች እና እውነታዎች

– ጅማ አባ ጅፋር አምና ወደ ሊጉ ሲያድግ ሀዋሳ ከተማን 2-0 በመርታት ጨዋታ ነበር ገዞውን የጀመረው። ሁለተኛው ዙር ላይ ግን ሀዋሳ ከተማ በሜዳው 1-0 አሸንፏል። ያ ሽንፈት የጅማ ብቸኛው የሁለተኛ ዙር ሽንፈትም ነበር።

– ሀዋሳ ከተማ እስካሁን ሀዋሳ ላይ አምስት ጨዋታዎችን ሲያደርግ ሽንፈት የገጠመው ሣምንት ከሲዳማ ጋር በተገናኘበት ጨዋታ ሲሆን ቀሪዎቹን በድል አጠናቋል።

– ጅማዎች ሦስት ጨዋታዎችን ከሜዳቸው ውጪ አድርገው አራት ነጥቦችን አሳክተዋል።

ዳኛ

– በመጀመሪያ ሳምንት አዳማ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም በአምስተኛው ሳምንት ሲዳማ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉትን ጨዋታዎች ዳኝቶ ሁለት የቢጫ ካርዶችን ያሳየው ፌደራል ድኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ይህን ጨዋታ እንዲመራ ተመድቧል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ጅማ አባ ጅፋር (4-3-3)                       

ዳንኤል አጄዬ

ያሬድ ዘውድነህ – ከድር ኸይረዲን – አዳማ ሲሶኮ – ኤልያስ አታሮ

ኄኖክ ገምቴሳ – ይሁን እንዳሻው – መስዑድ መሀመድ

ዲዲዬ ለብሪ – ማማዱ ሲዲቤ –ኤርሚያስ ኃይሉ

ሀዋሳ ከተማ (4-2-3-1) 

ሶሆሆ ሜንሳህ 

ዳንኤል ደርቤ – አዲስዓለም ተስፋዬ – ላውረንስ ላርቴ – ደስታ ዮሃንስ

አዳነ ግርማ  – መሣይ ጳውሎስ 

ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን – ታፈሰ ሰለሞን – ኄኖክ ድልቢ

እስራኤል እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *