የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-0 ድሬዳዋ ከተማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስረኛ ሳምንት አዳማ ላይ ድሬዳዋ ከተማን ያስናገደው አዳማ ከተማ 1-0 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“እንደነበረን የጨዋታ እንቅስቃሴ ውጤቱ ይገባን ነበር። ” ሲሳይ አብርሀም – አዳማ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ውጥረት የተሞላበት ነበር። ያለምንም ግብ ረጅም ደቂቃዎች መጫወታችን ተጫዋቾቼን ይበልጥ ጫና ውስጥ ከቷቸው ነበር። ሆኖም በመጀመሪያው አጋማሽ የነበረንን ክፍተት በሁለተኛው አጋማሽ ለውጥን በመግባታችን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ በተቆጠረች ግብ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለናል። ሶስት ነጥቡን በጣም እንፈልገው ነበር። ምክንያቱ ደሞ ድሬዳዋ በሜዳችን አሸንፎን ስለማያቅ ነው። ሳያቋርጥ የደገፊን እና አሰልጣኝ ባልደረቦቼን እንኳን ደስ ያለን እላለው።

ስለ ተጋጣሚያቸው

ድሬዳዋዎች ጥሩ ነበሩ። በመጀመሪያ አጋማሽ የግብ እድሎች ፈጥረው ነበር የ። በሙሉ ጨዋታ ክፍለ ጊዜውም የተከላካይ ክፍላቸው ጥሩ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ኋላ ይበልጥ መሳባቸው ለኛ ጥሩ እድል ፈጥሮልናል።

የከነዓን ቅያሪ
ከነዓን ላለፉት ሁለት ቀናት የጨጓራ ህመም አሞት ነበር። በልምምድ ላይም አልተሳተፈም። ዛሬም ወደ መልበሻ ክፍል ስንገባ አሞት በማየታችን ነው የቀየርነው።


“ያገኘነውን እድሎች ብንጠቀምባቸው ኖሮ ያሳብነውን እናሳካ ነበር ” ስምዖን ዓባይ – ድሬዳዋ ከተማ

ስለ ጨዋታው 

“ቡድናችን በቅጣት እንዲሁም በጉዳት ምክንያት ተጫዋቹችን እያጣ ያለ ቡድን ነው። ዛሬ በመልሶ ማጥቃት በመጫወት ወደመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ነጥብ ይዘን ለመውጣት በመፈለጋችን አቀራረባችንን ብንቀይርም ሳይሳካልን ቀርተናል። ያገኘነውን የግብ እድሎች ብንጠቀምባቸው ኖሮ ያሳብነውን እናሳካ ነበር።”

ስለ ተጋጣሚያቸው 

“አዳማዎች ኳስን ይዞ በመጫወት ከኛ ተሽለው ነበር። እኛ ደሞ በመልሶ ማጥቃት ላይ ነበር ተመርኩዘን የምንጫወተው። በግብ እድል በመፍጠር ከተጋጣሚያችን እኛ የተሻልን ነበርን። ሆኖም ያገኘነውም አጋጣሚ ሳንጠቀምበት ቀርተናል፤ ያም ዋጋ አስክፍሎናል።


ስለ ዳኝነቱ

” ዳኝነቱ ለኔ ጥሩ አልነበረም። ስለተሸነፍኩኝ አይደለም ግን ጥሩ አልነበረም። በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት ይገባን ነበር። ግን ዳኛው ምንም አላለም፤ ለእኔ የነበረው ዳኝነት አልተመቸኝም።”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *