“በእርግጠኝነት በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን እንቀለብሳለን” ዩሱፍ ዓሊ – ጅማ አባጅፋር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር በሜዳው በሀሳኒያ አጋዲር 1-0 ከተሸነፈ በኋላ የጅማው ምክትል አሰልጣኝ ዩሱፍ ዓሊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ስለ ጨዋታው

ጨዋታውን እንዳያችሁት 17 ተጫዋች ብቻ ነው ይዘን ለጨዋታው የቀረብነው። ስምንት ተጫዋቾችን በጉዳት አጥተናል። እንደዛም ሆኖ እኛ ከእነርሱ የተሻልን ነበርን። እነርሱ በረጃጅም ኳሶችን ሲጠቀሙ እኛ በተሻለ ሁኔታ ኳሱን ይዘን ነበር የተጫወትነው። በአንድ የመልሶ ማጥቃት ሂደት ጎሉን አስቆጠሩብን እንጂ ብልጫ ወስደንባቸዋል።

ስለቡድኑ ችግር

በመስመር የሚጫወቱ ተጫዋቾቻችን ጉዳት ላይ መሆናቸው እና ተደራራቢ ጨዋታዎች ቡድኑን አዳክሞታል። እንደዛም ሆነው ተጫዋቾቻችን ይወርዳሉ ብለን ብንጠብቅም የተሻለ ነገር ማሳየታቸው አስገርሞናል።

ስለ መልሱ ጨዋታ

በመቶ ፐርሰት እርግጠኝነት በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን እንቀለብሰዋለን። በጉዳት ያጣናቸው ተጫዋቾች ይመለሳሉ ። ቡድኑን አይተነዋል፤ ስለዚህ ተስፋ አለን። ውጤት ይዘን እንመለሳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *