“ለሃሳኒያ ምርጥ ዕለት ነበር” አሰልጣኝ ሚጉዌል አንሄል ጋሞንዲ

በካፍ ኮንፌዴሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ጅማ አባ ጅፋርን የገጠመው ሀሳኒያ አጋዲር 1-0 አሸንፎ ለመልሱ ጨዋታ እድሉን አስፍቶ ወጥቷል።

ከጨዋታው በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ አርጀንቲናዊው ሚጉዌል አንሄል ጋሞንዲ እና ብቸኛውን የድል ጎል በግሩም ሁኔታ ያስቆጠረው ዞሂር ቻውች ስለ ጨዋታው ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ለሃሳኒያ ምርጥ ዕለት ነበር” አሰልጣኝ አንሄል ጋሞንዲ

ጨዋታው እንዴት  ነበር?

ለሃሳኒያ ምርጥ ዕለት ነበር፡፡ የሚገባንን ድል አግኝተናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ጨዋታ ለማጫወት የማይበቃ ሜዳ ላይ ተጫውተን አሸንፈን ወጥተናል፡፡ በዚህ ሜዳና የአየር ሁኔታ ተጫውቶ ማሸነፍ በጣም ከባድ ነው፡፡ በመጀመሪያውም በሁለተኛውም ግማሽ የግብ እድሎችን ፈጥረናል፤ እዚ የመጣነው በቻልነው አቅም ጎል ለማግባት ነው ተሳክቶልናል ስለዚህ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡

በብዛት ረዣዥም ኳሶችን ስትጫወቱ ነበር፤ በሜዳው ምክንያት ይሆን? የጨዋታ ስትራቴጂያችሁስ ምን ነበር?

በቻልነው አቅም ጎል እንዳይቆጠርብን ኋላውን ዘግተን በሁለቱ የመጨረሻ ተከላካዮቻችን ኳስን ወደፊት በመጣል የግብ እድሎችን መፍጠርና ከተቻለም ግብ ማግባት ነበር ስትራቴጂያችን። የኋላ ተጫዋቾቻችን ድንቅ ነበሩ። በነገርህ ላይ ሃሳኒያ በሞሮኮ ሊግ ላይ ምርጥ የተከላካይ ክፍል ያለው ክለብ ነው፤ የተቃራኒ ቡድን አንድ እንኳ የሚያስፈራ የግብ ዕድል መፍጠር አልቻለም ተከላካዮቼ ድንቅ ነበሩ፡፡

ግቧን እንዴት አገኟት?

ምርጥ ጎል ነበረች፤ ተጫዋቹ በሊጋችንም ላይ ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዚህ የሚያስቆጥራቸው ምርጥ ምርጥ ጎሎች አሉት። የዛሬዋ  ግን ከአላማችን ጋር ድንቅ ነበረች፡፡

ሜዳው በጣም አስቸገራችሁ?

ሜዳው ለሁለታችንም አስቸጋሪ ነው፡፡ የተቃራኒው ቡድን እንኳ ቢሆን ከዚህ የተሻለ ሜዳ ቢያገኝ ከዚህ የተሻለ መጫወት ይችላል፡፡ የኛን ክለብ ጨዋታዎች ብታይ ረዣዥም ኳስ ይዞ የመጫወት ባህል የለንም፡፡ በሊጋችን ላይ በአጫጭርና በፈጣን ጨዋታ ነው የምንታወቀው። ሆኖም ግን እዚህ ሜዳ ላይ በዚህ የአየር ሁኔታ ምን ብለህ አጫጭር ኳስ ትጫወታለህ በፍጡም አትችልም ስለዚህ በጥንቃቄና በረዣዥም ለመጫወት ገባን፤ የምንፈልገውን አርገን ወጣን።

የመልሱ ጨዋታ ውጤት ምን ሊሆን ይችላል?

ገና ነው ማጣሪያው አላለቀም። በኛ ሜዳ ላይ የምናደርገውን 90 ደቂቃ መጠበቅ ያስፈልጋል። ነገር ግን እኛ ከነሱ የተሻለ እድል አለን፡፡ የመልሱ ጨዋታ ቀላል አይሆንም፤ ምክንያቱም የተሻለ ሜዳ ሲያገኙ እነሱም ከዚህ የተሻለ ሊጫወት እንደሚችሉ መገመት ትችላለህ። እዚህ ሜዳ ላይ ኳስ ተቆጣጥሮ መጫወት በጣም ይከብዳል፡፡

” እስካሁን ካገባኋቸው ጎሎች ሁሉ የምትበልጥ ምርጥ ጎሌ ናት” ዞሂር ቻውች

ስለ ጨዋታው 

በጣም ከባድ ጨዋታ ነበር፡፡ ሜዳው በጣም አስቸጋሪ ነበር፤ አላምዲሊላህ አሸንፈን ወጥተናል፡፡ የተሻልን ነበርን፤ በዚህ የአየር ሁኔታና በዚህ ሜዳ አሸንፎ መውጣት በጣም ከባድ ነው፡፡ ያሁኑ የመጀመሪያ ጨዋታ ነው የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በሜዳችን ነው ስለዚህ አሁን እኛ ከተጋጣሚያን ይልቅ የተሸ ለ የማለፍ ዕድል አለን፡፡

ስለ ጎሏ

እግር ኳስ እንደዚህ ነው፡፡ አዎ ግቧ ምርጥ ግብ ናት ጓደኛዬ ኳሷን ቀነሰልኝ እንዳገኘዋት ወደጎል ላኬያት ስትገባ ሳያት እኔም ልዩ ስሜት ነው የተሰማኝ። እስካሁን ካገባዋቸው ጎሎች ሁሉ የምትበልጥ ምርጥ ጎሌ ናት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *