” ከአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ጋር እስካሁን አልተለያየንም ” አቶ ተስፋይ ዓለም

ከትላንት በስቲያ በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስሑል ሽረ ያለ ዋና እና ረዳት አሰልጣኙ እንዲሁም ቡድን መሪው በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን ገጥሞ ያለ ጎል አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

በገብረኪሮስ አማረ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት እየተመራ ጨዋታውን ያደረገው ሽረ ከዋና አሰልጣኙ ዳንኤል ፀሐዬ እና ረዳት አሰልጣኙ በረከት ገብረመድኅን ጋር መለያየቱን መግለፃችን የሚታወስ ሲሆን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋይ ዓለም ክለቡ እስካሁን ከአሰልጣኞቹ ጋር እንዳልተለያየ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ” እስካሁን የአመራር ቦርዱ በዚህ ጉዳይ ላይ አልተሰበሰበም። ስለዚህ የአሰልጣኞቹ ጉዳይ ላይም ምንም አይነት ውሳኔ ላይ አልደረስንም።” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *