በፕሪምየር ሊጉ አንድ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል አንደኛው ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።

ድሬዳዋ ላይ በድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና መካከል እሁድ ጥር 19 ቀን 2011 ሊደረግ የነበረው ጨዋታ ነው ወደ ሌላ ጊዜ የተሸጋገረው። ለመራዘሙ መንስዔ የሆነውም በአካባቢው ያለው ወቅታዊ አለመረጋጋት መሆኑ ታውቋል።

የ13ኛ ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች በተያዘላቸው መርሐ ግብር እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።

እሁድ ጥር 19 ቀን 2011

ደቡብ ፖሊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ
ወልዋሎ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፋሲል ከነማ ከ አዳማ ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና ከ ጅማ አባ ጅፋር

ሰኞ ጥር 20 ቀን 2011

ወላይታ ድቻ ከ ባህር ዳር ከተማ
ደደቢት ከ ስሑል ሽረ
መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መከላከያ ከ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ሰኞ የነበረው መርሐ-ግብር ወደ እሁድ 4:00 መለወጡን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *