የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

የመጀመሪያው ዙር በቀጣዩ ሳምንት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛው የውድድር አጋማሽ መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋ ባሳወቀው መሰረት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መጋቢት 01 ይጀምራል። በዚህ መሰረት በ16ኛው ሳምንት ከሚደረጉ ጨዋታዎች ውስጥ አምስቱ መጋቢት 1 ላይ ሲከናወኑ ቀሪዎቹ ሦስት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጋቢት 8 ላይ ይደረጋሉ። በወጣው መርሐ ግብር መሰረትም የዘንድሮው ውድድር ሰኔ 9 ላይ ፍፃሜውን እንደሚያገኝ ይጠበቃል።

የ16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር

እሁድ መጋቢት 01 ቀን 2011

ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ
ወልዋሎ ዓ/ዩ ከ ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
መከላከያ ከ ደቡብ ፖሊስ

እሁድ መጋቢት 08 ቀን 2011

ጅማ አባ ጅፋር ከ አዳማ ከተማ
ፋሲል ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
ደደቢት ከ መቐለ 70 እንደርታ

– ሙሉውን ፕሮግራም በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *