መከላከያ የአማካይ ተጫዋቹን ኮንትራት አራዘመ

ዘንድሮ በመከላከያ ጥሩ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ዳዊት እስጢፋኖስ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በቡድኑ የሚቆይበትን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል።

ከፋሲል ከነማ ጋር አምና ከስድስት ወር ቆይታ በኋላ በስምምነት መለያየቱን ተከትሎ በአንድ ዓመት ኮንትራት ወደ ቀድሞ ክለቡ መከላከያ ያመራው ዳዊት እስጢፋኖስ የኮንትራት ዘመኑ ዛሬ የሚጠናቀቅ ቢሆንም ክለቡ ባቀረበለት ጥያቄ መሰረት እርሱም ፍቃደኛ በመሆኑ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ከመከላከያ ጋር የሚያቆየውን ፊርማውን አኑሯል።

ከቅርብ ጨዋታዎች ጀምሮ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ የሚገኘው ዳዊት በ1990ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእግርኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኋላ በመከላከያ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኤሌክትሪክ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ተጫውቶ አሳልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *