ስሑል ሽረ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

ባሰናበቷቸው በርካታ ተጫዋቾች ምትክ ተጫዋቾች በማስፈረም የተጠመዱት አዲስ አዳጊዎቹ ስሑል ሽረዎች ላለፉት ሁለት ዓመታት በጅማ አባጅፋር ቆይታ ያደረገው እና ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያልፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካደረጉት ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ብሩክ ተሾመን አስፈርመዋል።

በርካታ የአማካይ ክፍል ተጫዋቾች የለቀቁት ስሑል ሽረዎች ባሳለፍነው ዓመት ከጅማ አባጅፋር ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አንስቶ በዚህ ዓመት መጀመርያ ከቡድኑ ጋር በስምምነት የተለያየው ብሩክ ተሾመን ጨምሮ ዩጋንዳዊው ያሰር ሙገርዋን ማስፈረማቸውን ተከትሎ በመጀመርያው ዙር የታየባቸውን የአማካይ ክፍል ተጫዋቾች እጥረት ይቀርፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከስሑል ሽረ ጋር በተያያዘ ዜና ባሳለፍነው ዓመት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ድንቅ ዓመት ላሳለፈው ጋናዊው ጋይሳ አፓንግ ቢስማርክ እና ለኮትዲቫራዊ ሳሊፍ ፎፋና የሙከራ ዕድል መስጠታቸው ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *