ፌዴሬሽኑ ለሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የቅጥር ማስታወቂያ አወጣ

በጃፓኗ መዲና ቶኪዮ የሚከናወነው የ2020 ኦሊምፒክ ላይ በሴቶች እግርኳስ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን ከዩጋንዳ ጋር በመጋቢት ወር መጨረሻ የሚያከናውን ሲሆን ለዚህም ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ከወዲሁ አሰልጣኝ ለመቅጠር ዛሬ የቅጥር ማስታወቂያ ወጥቷል።

ፌዴሬሽኑ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ላይ ከተጠቀሱ መስፈርቶች መካከል በሴቶች ሊግ ላይ ሦስት እና ከዚያ በላይ ዓመታት የማሰልጠን ልምድ እንዲሁም ውጤት ያላት፣ ከካፍ የስራ ቋንቋዎች አንዱን የምትናገር፣ 10ኛ ክፍል በላይ የሆነች እና ከቢ ላይሰንስ በላይ ያላት፣ የአስተዳደራዊ እና የስልጠና ዕቅዷን የምታቀርብ እና በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነች ይጠቀሳሉ።

ተወዳዳሪዎች መመዝገብ የሚችሉት እስከ የካቲት 29 እንደሆነ ሲገለፅ በመጋቢት ወር ላይ አሸናፊዋ አሰልጣኝ ይፋ እንደምትደረግ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ከመጋቢት 23 እስከ መጋቢት 30 ባሉት ቀናት በደርሶ መልስ የምታከናውን ሲሆን የመጀመርያው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል። ዩጋንዳን ካለፈች ደግሞ በቀጣዩ ዓመት መጀመርያ ከካሜሩን ጋር በሁለተኛ ዙር ማጣርያ የምትገናኝ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *