ከፍተኛ ሊግ | አውስኮድ ከመፍረስ ድኗል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሀ ተደልድሎ ውድድሩን እያደረገ የሚገኘው አውስኮድ ባሳለፍነው ሳምንት የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ከመፍረስ አደጋ እንደዳነ ተረጋግጧል።

በዘንድሮ የውድድር ዘመን በከፍተኛ የውጤት ቀውስ ውስጥ በመገኘት አንድ ድል ብቻ አስመዝግቦ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው አውስኮድን ለማፍረስ ያሰቡት የክለቡ አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በውድድር ላይ እንደማይቆዩ የሚገልፅ ደብዳቤ ለመላክ መቃረባቸው እና ተጫዋቾቻቸውን ለመበተን እንደወሰኑ ሲሰማ ቆይቷል።

ይህንን ውሳኔ በመቃወም የክለቡ ደጋፊዎች፣ የቀድሞ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች አመራሮቹ ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ጫና በማሳደራቸው ዛሬ ክለቡ እየተሳተፈበት የሚገኘውን ዓመታዊ ውድድር እንደሚጨርስ አሳውቋል። ምንም እንኳን ክለቡ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ጨዋታዎችን እያደረገ ውድድር ላይ ይቆይ እንጂ ዘለቄታዊ ህልውናው አሁንም አደጋ ላይ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *