ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ጅማ አባ ጅፋር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ከነገ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል የአባ ጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

በአምናው የውድድር ዓመት እስከመጨረሻው ሳምንት ተናንቀው የቆዩት ጅማ አባ ጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነገ የዘንድሮ የሁለተኛውን ዙር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ባሳለፍነው ሳምንት መከላከያ ላይ አራት ጎሎችን ያዘነቡት ጅማዎች ወደ 7ኛ ደረጃ ከፍ ማለት ችለዋል። ከዚህ ባለፈም ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ግብ አለማስተናገዱ ከአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጋር ለተለያየው ክለብ ጥሩ የሚባል ጉዳይ ነው።  በመከላከያው ጨዋታ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ያመቻቸው መስዑድ መሀመድ መልካም አቋም ላይ መገኘት እና የኦኪኪ አፎላቢ የወረቀት ጉዳዮችን ጨርሶ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆን ደግሞ ለአባጅፋሮች ሌሎች መልካም ዜናዎች ናቸው። ከዚህ ውጪ ቡድኑ በጉዳትም ሆነ በቅጣት የሚያጣው ተጫዋች የሌለ ሲሆን ዘሪሁን ታደለም ከጉዳት መልስ 18ቱ ውስጥ እንደሚካተት ይጠበቃል። ጅማዎች በጦሩ ጨዋታ ላይ እንዳሳዩት ሁሉ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ተጋጣሚ የመከላከል ቅርፁን ሳይዝ ወደ አደጋ ክልል መድረስ እና በጥቂት ዕድሎች ግቦችን የማስቆጠርን ብቃት ነገ መድገም ከቻሉ ለፈረሰኞቹ ፈተና የሚሆኑበት ዕድል የሰፋ ነው።

ከሦስት ጨዋታዎች ቆይታ በኋላ አዳማ ከተማን ድል ባደረጉበት ጨዋታ ግብ ወደ ማስቆጠሩ የተመለሱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከመቐለ ጋር ያላቸውን ልዩነት በጥቂቱም ቢሆን ቀንሰዋል። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኝ ስትዋርት ሀል እንደሰጡት አስተያየትም ቡድኑ ግብ በእጅጉ ያስፈልገው ነበር። ከዛ ውጪ የፊት አጥቂው ሪቻርድ አርተር በፍጥነት ከቡድኑ ጋር መላመድ እና ለአማካይ ክፍሉ ቀርቦ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ለተከላካዮች ፈታኝ መሆኑ በበጎው የሚነሳ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰዒድ እና መሀሪ መናን በጉዳት በኃይሉ አሰፋን ደግሞ በቅጣት የሚያጣ ሲሆን የጌታነህ ከበደ መሰለፍም አጠራጣሪ ሆኗል። ከዚህ ውጪ ጉዳት ላይ የሰነበተው ሳላዲን በርጌቾ ወደ ሜዳ ሲመለስ ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታሲ በብሔራዊ ቡድን ግዳጅ ምክንያት ጨዋታው ያልፈዋል። ፈረሰኞቹ ከበላያቸው ይሉት መቐለ እና ሲዳማም ከሜዳ ውጪ ከበድ ይሉ ፈተናዎች የሚጠብቋቸው በመሆኑ ሙሉ ነጥብን ማሳካት ከቻሉ በዋንጫው ፉክክር ውስጥ ያላቸውን ተስፋ ማለምለም ይችላሉ።

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– ከአምና ጀምሮ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙባቸው ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ጊዜ ሜዳው ላይ 3-0 እና 2-0 ሲያሸንፍ ጅማ ላይ በተከናወነው አንድ ጨዋታ 1-1 ተለያይተዋል።

–  ቻምፒዮኖቹ በሜዳቸው ስምንት ጨዋታዎችን ሲያደርጉ አንዴም አልተሸነፉም  አራት ጊዜ ድል ሲያደርጉ አራት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል። ከድሬዳዋው የ3-3 ጨዋታ በኋላም ቡድኑ በአራት ጨዋታዎች ጅማ ላይ ግብ አላስተናገደም። 

– ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን ከአዲስ አበባ ስታድየም ውጪ ስምንት ጨዋታዎችን ሲያደርግ ሦስቴ ድል የቀናው ሲሆን ሁለት በአቻ ሦስት ጊዜ ደግሞ በሽንፈት ተመሷል።
                         
ዳኛ

– በርካታ ጨዋታዎች (8) በመዳኘት ቀዳሚ የሆነው ኢንተርናሽናል ዳኛ አማኑኤል ኃይለሥላሴ ይህን ጨዋታ የመንራት ሀላፊነዮት ተሰጥቶታል። በአማካይ በጨዋታው 3.75 የሾቢጫ ካርዶችን የሚመዘው አማኑኤል ሀለት የፍፁም ቅጣት ምቶችንም ሰጥቷል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ጅማ አባ ጅፋር (4-3-3)                       

ዳንኤል አጄዬ

ዐወት ገ/ሚካኤል – መላኩ ወልዴ – አዳማ ሲሶኮ – ኤልያስ አታሮ                                                     

                               
ይሁን እንዳሻው – አክሊሉ ዋለልኝ – መስዑድ መሀመድ

ዲዲዬ ለብሪ – ማማዱ ሲዲቤ – አስቻለው ግርማ

ቅዱስ ጊዮርጊስ (3-5-2)

ፓትሪክ ማታሲ

አስቻለው ታመነ  – ምንተስኖት አዳነ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ 

አብዱልከሪም መሀመድ – ሙሉዓለም መስፍን – ናትናኤል ዘለቀ – ኄኖክ አዱኛ

ሃምፍሬ ሚዬኖን

ሪቻርድ አርተር – አቤል ያለው

                                             

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *