እድሉ ደረጄ እሁድ ወደ ስፔን ያቀናል

በስፔኗ ባርሴሎና የአሰልጣኞች ትምህርት ከሚሰጠው mbp ከተሰኘ የትምህርት ተቋም ጋር ባደረገው ግኑኝነት ነው ለአንድ ወር የሚቆየውን የትምህርት ለመከታተል እሁድ ወደ ስፔኗ ባርሴሎና ያቀናል።

ለጉዞ እና ለቪዛ የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ 500 ዩሮ ከራሱ ወጪ በማድረግ ቢከፍልም ለትምህርት፣ ለትራንስፖርት እና ለሌሎች ጉዳዮች ልዩ ልዩ ወጪዎች ከ3000 ዩሮ በላይ ለመክፈል የአቅም ውስንነት እንደነበረበት መዘገባችን ይታወቃል። የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠንም የተለያዩ አካላት ድጋፍ ያደረጉለት በመሆኑ እሁድ 05:00 ላይ ወደ ስፔን ያቀናል።

እድሉ ደረጄ ድጋፍ ያደረጉለትን አካላት በሙሉ አመስግኖ በተለይ የትምህርት ቤት ክፍያውን ሙሉ ወጪ የኢትዮጵያ ቡና እና ደጋፊ ማኅበሩ በመሸፈናቸው ከፍተኛ ምሰጋና እንደሚያቀርብ ገልጿል። በባርሴሎና በሚኖረው ቆይታም መሠረታዊ የሚባሉ የእግርኳስ ስልጠናዎች በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ትምህርቱን እንደሚከታተል ተናግሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡