ፌዴሬሽኑ ብሩክ የማነብርሀንን ቀጥቷል 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉትን ጨዋታ የመሩት ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሀን ላይ የቅጣት ውሳኔ እንዳሳለፈ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። 

በወላይታ ድቻ 2-1 አሸናፊነት በተጠናቀቀው ጨዋታ የመጀመርያው የወላይታ ድቻ ጎል የተቆጠረበት መንገድ የዳኛው ስህተት የተንፀባረቀበት ነው ብሎ በማመኑ ብሩክ የማነ ብርሀንን ለቀጣይ ሁለት ወራት እንዳይዳኙ አግዷቸዋል። 

የቅተት ዝርዝሩ ይህንን ይመስላል