ደደቢት በቅዳሜው ጨዋታ ዙርያ ያለውን አቋም አሳወቀ

ደደቢት ባለፈው ሳምንት ፋሲል ከነማን ባስተናገደበት ጨዋታ ስለተፈጠረው ስርዓት አልበኝነት ያለውን አቋም በደብዳቤ ለፌደሬሽን አሳወቀ።

ለፌደሬሽኑ ስለላኩት ደብዳቤ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የክለቡ ፕሬዝደንት አቶ ሚካኤል ዓምደመስቀል ክለቡ ሙሉ ኃላፊነት እንዲወስድ ተናግረዋል። ” ጨዋታው ካለቀ በኃላ ጉዳዩ በጣም እንደሚያሳዝን እና መደገም እንደሌለበት ገልፀን ኃላፊነቱም ደደቢት ሙሉ ለሙሉ እንደሚወስድ ለጨዋታው ኮሚሽነር ገልፀናል። አሁን ጉዳዩ ከሶስተኛ ወገን ጋር ሲያያዝ እሱን ተከትለን የሰጠነው ኃሳብ አይደለም። ልክ ጨዋታው እንዳለቀ ለጨዋታው ኮምሽነር አቋማችን አስረግጠን ተናግረናል።” ብለዋል።

አቶ ሚካኤል አክለውም ደደቢት በቅድመ ጨዋታ ደጋፊ የለኝም ኃላፊነት አልወስድም ብለዋል የተባለው ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልፀዋል። “በሜዳችን እየተጫወትን እንዴት ነው ደጋፊ የለንም ማለት የምንችለው። ባለፉት ጨዋታዎችም እኮ ደጋፊዎች ነበሩን። በርካታ የመቐለ ማልያ የለበሱ ደጋፊዎች ነበሩ ለተባለውም እኛ ለደጋፊያችን ማልያ ለማቅረብ አቅም ስሌለለን ደጋፊው የመቐለም የሌላም ክለብ ማልያ አድርጎ ነው የሚገባው” ብለዋል።

ክለቡ ለፌዴሬሽን የላከው ደብዳቤ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡