ቻን 2020| የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዝግጅት ቦታ ለውጥ ተደረገበት

ለ2020 የቻን ውድድር ማጣርያ ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመርያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አስቀድሞ ከተያዘው ቦታ ለውጥ ማድረጉ ታውቋል።

ቡድኑ አስቀድሞ የመልሱን ጨዋታ በሚያደርግበት ድሬዳዋ ዝግጅት እንደሚጀምር ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ቦታውን በመቀየር ነገ በአዳማ ከተማ ዝግጅት የሚጀምር ይሆናል። ወደ ጅቡቲ እስከሚያቀናበት ጊዜ ድረስ ዝግጅቱን በመቀጠልም ከመጀመርያው ጨዋታ በኋላ በድሬዳዋ ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅቱን ይቀጥል ተብሏል።

ብሔራዊ ቡድኑ በቅርቡ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ሐምሌ 19፣ የመልሱን ደግሞ ከሐምሌ 26 እስከ 28 ባሉት ቀናት ያከናውናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡