ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ነሐሴ ወር ላይ ይደረጋል

በሁለት ምድቦች ተከፍሎ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድሩን ነሀሴ ላይ በአዳማ ከተማ ያካሄዳል።

በአጠቃላይ 19 ክለቦችን በሁለት ምድቦች ሲያወዳድር በቆየው በዚህ ውድድር ከምድብ ሀ ሀዋሳ ከተማ፣ ከምድብ ለ ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚ ሆነው አጠናቀዋል። ከየምድቡ እስከ አምስተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ አጠቃላይ 10 ቡድኖች ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ የሚያመሩ ሲሆን ከነሐሴ 5 ጀምሮ በሚደረገው ውድድርም አጠቃላይ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል።

ከውድድሩ ጋር በተያያዘ ከሳምንት በፊት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጨረሻው ሳምንት ከሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ዙርያ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ላይ ያለውን ቅሬታ ጨምሮ ተገቢ ፍትህ ካልተሰጠው ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ራሱን በማግለሉ በውድድሩ ላይ የመሳተፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው።© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡