ኢትዮጵያውያን ዳኞች የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታን ይመራሉ

የ2019/20 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ በቀጣዩ ሳምንት ሲጀምር ኢትዮጵያን ዳኞች ጨዋታ ይመራሉ።

የግብፁ ኃያል ክለብ ዛማሌክ ከሶማሊያው ዴከዳ ጋር በቀጣይ ሳምንት እሁድ የሚያደርጉትን የመጀመርያ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ፣ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ትግል ግዛው እና ሸዋንግዛው ተባበል ሲመሩ አራተኛ ዳኛ በመሆን አማኑኤል ኃ/ሥላሴ እንዲሆኑ ተመድበዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በአፍሪካ መድረክ ውድድሮችን በዋና ዳኝነት ሲመራ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡