ሀዋሳ ከተማ የመጀመርያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጫዋቹ ሄኖክ አየለን የመጀመርያው ፈራሚ በማድረግ ወደ ዝውውሩ ገብቷል።

ሄኖክ ሄኖክ ከዚህ ቀደም በሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ እና በደቡብ ፖሊስ የተጫወተ ሲሆን ባለፈው ዓመት አጋማሽ ዲላ ከተማን ለቆ ወደ ደቡብ ፖሊስ ካመራ በኋላ በተለይም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከደቡብ ፖሊስ ጋር ከጉዳት ነፃ የሆነ የተሳካ ቆይታ አድርጓል። በግሉም 12 ጎሎችን በማስቆጠር በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ዝርዝር ውስጥ መካተት የቻለ አጥቂ ነው።

በስብስቡ ውስጥ ወጣቶቹ እስራኤል እሸቱ እና መስፍን ታፈሰን በያዘው ሀዋሳ ከተማ ሄኖክ ለመጀመርያ ተሰላፊነት ፉክክር ይጠብቀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡