ኤፍሬም አሻሞ ቻምፒዮኖቹን ለመቀላቀል ተስማማ

ባለፈው ዓመት ከወልዋሎ ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው የመስመር ተጫዋቹ ኤፍሬም አሻሞ መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል ተስማማ።

በቀጣይ ወር ላላቸው የአፍሪካ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማዘዋወር የተጠመዱት 70 እንደርታዎች ከኤፍሬም አሻሞ ጋር መስማማታቸው ሲረጋገጥ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት በይፋ ከተጫዋቹ ጋር እንደሚፈራረሙ ለማወቅ ተችሏል።

ባለፈው ዓመት ከወልዋሎ ጋር በግሉ ጥሩ ዓመት ያሳለፈው የመስመር አማካዩ ከዚህ በፊት በሐረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ እና ደደቢት መጫወቱ ሲታወስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መለያ ለብሶም በጥቂት ጨዋታዎች ላይ ተሳትፏል።

በቀጣይ ወር መጀመርያ የኢኳቶሪያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚን የሚገጥሙት ምዓም አናብስት በቀጣይ ሁለት ቀናት ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚመለሱ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡