ቻን 2020| የኢትዮጵያ ተጋጣሚ በወዳጅነት ጨዋታ አሸነፈች

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ትላንት በወዳጅነት ጨዋታ ሶማሊያን ገጥሞ 1-0 አሸንፏል።

የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን በማጣርያው ከዩጋንዳ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በጅቡቲ የሚያከናውን ሲሆን ለዝግጅት ይረዳው ዘንድ ከጎረቤት ሀገር ጋር ጨዋታውን አድርጓል። ሐምሌ 19 ኢትዮጵያን በመጀመርያ ጨዋታ የምታስተናግደው ጅቡቲ በስታድ ዱ ቪሌ ያደረገችውን ጨዋታ በ59ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረ እና ኳስ በግንባር ተገጭቶ በተቆጠረ ጎል 1-0 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የሚታወቅ ቢሆንም የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ አልቻለም። በነገው ዕለትም ጨዋታውን ወደሚያደርግበት ጅቡቲ እንደሚያመራ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡