በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ያደጉ ቡድኖች ታውቀዋል

በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ያለፉ ቡድኖች ታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት ከምድብ 1-4 የሚገኙ ቡድኖች ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን የሚከተሉት ውጤቶች ተመዝግበዋል፡-

ሞጣ ከተማ 3-0 ሠመራ ሎጊያ
ሐውዜን ከተማ 1-0 ኩርሙክ ከተማ
ዳውሮ ሀላላ 1-1ባምባሲ ከተማ
ሲልቫ 3-0 ሐረር ዩናይትድ
ሸዋሮቢት 2-2 ሀሳሳ ከተማ
አዲስ ከቴ 0-3 ቦዲቲ ከተማ
ሙኩይ 2-0 መንጌ ቤኒሻንጉል
ዓደዋ ውሃ አ. 1-3 ደጋን ከተማ

* ሰመራ ሎጊያ ሁለት ጨዋታዎች ከተጫወተ በኋላ ከውድድሩ አቋርጦ የወጣ በመሆኑ በቀሪው ሁለት ጨዋታ ፎርፌ እንዲሰጥ ተወስኗል።

ከምድብ 5-8 ያሉት ቡድኖች ጨዋታዎች ትላንት ሲጠናቀቁ በምድብ 6 ቀዳሚ ሆኖ አጠናቆ የነበረው ጂኮ ከተማ በተጭበረበረ መታወቂያ ተጫዋች ማሰለፉ በመረጋጡ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ተሰርዘው በምትኩ አኳ ድሬ አልፏል። በምድብ 1 ደግሞ አሳይታ ከተማ አንድ ጨዋታ ብቻ አድርጎ ከውድድሩ በመውጣቱ የተመዘገበው ውጤት ተሰርዞ በሦስት ቡድኖች መካከል የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤቶች ብቻ እንዲመዘገቡ ተደርጓል።

ወደ አንደኛ ሊግ ለማደግ የሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች

ዓርብ ሐምሌ 26 ቀን 2011

3:00| ሐውዜን ከተማ ከ ኮረም ከተማ (አበበ ቢቂላ)
3:00| መኩይ ከ ኤጀሬ ከተማ (ወጣት ማዕከል)

5:00| መከላከያ ከ ሲልቫ (አበበ ቢቂላ)
5:00| ሀሳሳ ከተማ ከ አኳ ድሬ (ወጣት ማዕከል)

7:00| ቦዲቲ ከተማ ከ ሾኔ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
7:00| ም/ዐባያ ከ ፈራውን ከተማ (ወጣት ማዕከል)

9:00| ደጋን ከተማ ከ አቃቂ ማዞርያ (አበበ ቢቂላ)
9:00| ኣብዲ ሱሉልታ ከ ሞጣ ከተማ (ወጣት ማዕከል)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡