ፈረሰኞቹ የስድስት ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዘሙ

ዛሬ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የስድስት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዘሙ

ለቀጣይ የውድድር ዓመት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት የጀመሩት ፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂው ለዓለም ብርሃኑ፣ ተከላካዮቹ ሰልሃዲን በርጊቾ እና አብዱልከሪም መሐመድ፣ አማካዮቹ ናትናኤል ዘለቀ እና ጋዲሳ መብራቴ እንዲሁም አሜ መሐመድን ውል ያደሱ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች ለቀጣይ ሁለት ዓመት በክለቡ የሚያቆያቸው ውል ነው ያሰሩት።

በቀጣይ ቀናት የአሰልጣኝ ቅጥር ይፈፅማሉ ተብለው የሚጠበቁት ጊዮርጊሶች ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ሲጠበቅ ከክለቡ ጋር የሚለያዩ ተጫዋቾች እንደሚኖሩም ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡