አዳማ ከተማ የከፍተኛ ሊጉን ኮከብ ጎል አስቆጣሪ አስፈረመ

አሸናፊ በቀለን ዳግም የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ከቀጠረ በኋላ ዝውውሮችን እየፈፀመ የሚገኘው አዳማ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ስንታየሁ መንግስቱን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በወላይታ ድቻ ከወጣት ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ መጫወት የቻለው ረጅሙ አጥቂ ስንታየሁ ለሁለት የውድድር ዓመታት በሀላባ ከተጫወተ በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን 15 ጎሎችን በማስቆጠርም የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። አሁን ደግሞ ወደ አዳማ ከተማ በሁለት ዓመት ውል መቀላቀሉ ታውቋል።

ዐምና በአጥቂ አማራጭ እጥረት የተቸገረው አዳማ ከተማ በክረምቱ ከስንታየሁ በተጨማሪ ሐብታሙ ወልዴን በማስፈረም እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን ሶሬሳ ዱቢሳን በማሳደግ ቦታውን አጠናክሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡