ወልቂጤ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረሙን ቀጥሏል

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ወልቂጤ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በማጠናቀቅ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ቁጥር ዘጠኝ አድርሷል።

ጫላ ተሺታ ወደ ወልቂጤ ለማምራት ከተስማሙት አንዱ ነው። በ2008 በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባሳየው ብቃት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ወጣቱ የመስመር አጥቂ በሻሸመኔ ከተማ እና ሰበታ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ያለፉት ሁለት የውድድር ዘመናትን ደግሞ በሲዳማ ቡና አሳልፏል።

አማካዩ ሙሀጅር መኪ ሌላው ወልቂጤን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ረጅም ጊዜ የቆየው አማካዩ እንደ ጫላ ሁሉ በአንድ ዓመት ውል ቡድኑን መቀላቀሉ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡