ሲዳማ ቡና የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጓዳኝ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የፈቱዲን ጀማል እና ሐብታሙ ገዛኸኝን ውል አራዝሟል።

የቀድሞ የአዶላ ወዩ፣ ሀላባ ከተማ እና ወላይታ ድቻ የመሀል ተከላካይ ፈቱዲን ጀማል ድቻን 2009 ክረምት ላይ ከለቀቀ በኋላ በሲዳማ ቡና ጥሩ ሁለት የውድድር ዓመታት አሳልፏል።

ሌላኛው ውሉን ያራዘመው የአጥቂ እና የመስመር ተጫዋቹ ሐብታሙ ገዛኸኝ ነው። ደቡብ ፖሊስን ለቆ ሲዳማን ከተቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ መሻሻል ያሳየው ሐብታሙ በተለይ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጥሩ አቋም ከማሳየቱ ባሻገር ለብሔራዊ ቡድን መመረጥም ችሏል።

ሲዳማ ቡና እስካሁን የዘጠኝ ተጫዋቾች ውል ሲያድስ ሁለት አዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡