ከፍተኛ ሊግ | ኢኮስኮ አዲስ አሰልጣኝ ሲቀጥር ገላን ከተማ ደግሞ ውል አራዝሟል

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተወዳዳሪ የሆነው ገላን ከተማ የአሰልጣኝ ዳዊት ታደሰን ውል ሲያራዝም በምድብ ለ የሚገኘው ኢኮስኮ ደግሞ በጸሎት ልዑልሰገድን ቀጥሯል።

ኢኮስኮ ከዋና አሰልጣኙ ደግአረግ ይግዛው ጋር ከተለያየ በኋላ የአሰልጣኝ ቅጥር አውጥቶ የነበረ ሲሆን ዛሬ ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሠረትም ለመጨረሻ እጩነት ያቀረባቸው ሦስት አሰልጣኞችን ካወዳደረ በኋላ ወጣቱ አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድን ሾሟል።

ከ1999 ጀምሮ በበቆጂ ከተማ፤አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፤ አዲስ አበባ ከተማ ፤ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ እና ኢትዮጵያ መድን የሰሩት አሰልጣኝ በፀሎት በ2010 ቢሾፍቱን ወደ ከፍተኛ ሊግ ሲያሳድጉ በ2011 ደግሞ መድንን ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማሳደግ ተቃርበው ነበር።

በተያያዘ የከፍተኛ ሊግ ዜና በ2011 ውድድር ዓመት ወደ ከፍተኛ ሊግ ካደጉት መካከል ጥሩ ቡድን ይዞ በመቅረብ ዓመቱን ያሳለፈው ገላን ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ያሳደገው ወጣቱ አሰልጣኝ ዳዊት ታደሰን ለተጨማሪ ዓመት ለማስቀጠል ተስማምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡