በመቐለ የሚካሄደው ዓመታዊ የፉትሳል ውድድር ተጀመረ

በየዓመቱ በመቐለ ባሎኒ ትንሿ ሜዳ ላይ የሚካሄደው ዓመታዊ የፉትሳል ውድድር ዛሬ ተጀምሯል።

ላለፉት ሰባት ዓመታት በተለያዩ አዘጋጆች ሲካሄድ የቆየው ይህ ውድድር የዘንድሮው ውድድር ሰምንተኛው ሲሆን ገና ከጅማሮው የከተማው እግር ኳስ ተከታታይ ቀልብ የሳበው ይህ ውድድር ከፕሪምየር ሊግ ፣ ከፍተኛ ሊግ እና ብሄራዊ ሊግ የተወጣጡ ተጫዋቾች እና በርካታ ተስፈኛ ተጫዋቾች እየተሳተፉበት እንደሚገኝና በርካታ ዓላማዎች አንግቦ የተዘጋጀ ውድድር እንደሆነ የውድድሩ አዘጋጅ አቶ ተስፉ ገ/ኢየሱስ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

“ባለፉት ዓመታት ከዞኑ ጋር በጋራ ሆነን ነበር ስናዘጋጀው የቆየነው። ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን በራሴ ተነሳሽነት ውድድሩን በተሻለ ጥራት ለማካሄድ ነው የወሰንኩት። የውድድሩ ዋና ዓላማ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት እና ለከተማው ወጣት ጥሩ የመዝናኛ አማራጭ ለመፍጠር ነው ” ብለዋል።

የከተማው የእግር ኳስ ተመልካች በትንሿ ስታዲየም ተገንቶ ውድድሩን እንዲከታተል ጥሪያቸው ያስተላለፉት የውድድሩ አዘጋጆች ይህ ውድድር በቀጣይ ዓመታትም በተሻለ አቀራረብ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡