ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ ፈራሚው ዘላለም ኢሳይያስን አድርጓል።

የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በደቡብ ፖሊስ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በግሉ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን በሊጉ በርካታ ጎል የሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዱ ነበር። በደቡብ ፖሊስ የእግርኳስ ህይወቱን ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ በማድረግ ዐምና ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመልሶ የነበረው ዘላለም በአንድ ዓመት ውል በተቀላቀለው ወላይታ ድቻ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር የሚገናኝ ሲሆን በአብዱልሰመድ ዓሊ እና ፍፁም ተፈሪ መልቀቅ የተፈጠረውን የአማካይ ክፍል ክፍተት ለመሸፈን ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡