ስሑል ሽረ አራተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል


ስሑል ሽረ አማካዩ አክሊሉ ዋለልኝን በማስፈረም የአዲስ ተጫዋቾች ቁጥርን አራት አድርሷል።

ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ መጫወት የቻለው አማካዩ በኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድንም በአምበልነት የተጫወተ ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና ሁለት የውድድር ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በጅማ አባጅፋር ቀይታ አድርጓል። አሁን ደግሞ በአንድ ዓመት ውል ማረፊያው ስሑል ሽረ ሆኗል።

ስሑል ሽረ አስቀድሞ በረከት ተሰማ፣ ወንደሰን አሸናፊ እና አዳም ማሳላቺን ወደ ክለቡ መቀላቀሉ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡