ወልቂጤ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የአራት ነባሮችን ውል አድሷል

ወልቂጤ ከተማ አሳሪ አልማህዲን ወደ ቡድኑ ሲቀላቅል አራት ነባር ተጫዋቾች ውላቸው ታድሶላቸዋል።

ከዚህ ቀደም ለወልዋሎ እና ድሬዳዋ ከተማ የተጫወተው አሳሪ ከግማሽ ዓመት ጀምሮ ለስሑል ሽረ የተጫወተ ሲሆን አሁን ደግሞ ማረፊያውን ወልቂጤ በማድረግ የቡድኑ 10ኛ ፈራሚ ሆኗል። አሳሪ በመሐል እና መስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ መጫወት ይችላል።

በተያያዘ ዜና የወልቂጤ ቡድን አራት ነባር ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል። 13 ጎሎችን በከፍተኛ ሊጉ ያስቆጠረው አጥቂው አህመድ ሁሴን፣ በውድድር ዘመኑ ድንቅ ብቃት ሲያሳይ የነበረው ተስፈኛው አማካይ አብዱልከሪም ወርቁ፣ ተከላካዩ መሐመድ ሻፊ እና ካሜሩናዊው ግብጠባቂ ቤሊንጋ ኢኖህ ውል ያራዘሙት ተጫዎቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡