ሀዋሳ ከተማ የአራት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ሀዋሳ ከተማ ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ አራት ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

ሄኖክ አየለ እና አለልኝ አዘነን ወደ ቡድኑ የቀላቀለውና የውጪ ዜጎቹ ላውረንስ ላርቴ፣ ሶሆሆ ሜንሳህ እና ያኦ ኦሊቨርን እንዲሁም የወጣቱ መስፍን ታፈሰን ውል ማራዘም የቻለው ሀዋሳ ከተማ አሁን ደግሞ ወደ ሌሎች የቡድኑ ተጫዋቾች ፊቱን በማዞር የአራቱን ውል አድሷል። ለረጅም ጊዜ በቡድኑ የቆዩት ተከላካዮቹ አዲስዓለም ተስፋዬ እና ዳንኤል ደርቤ እንዲሁም አማካዩ አስጨናቂ ሉቃስ እና ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ በክለቡ ቆይታን ለማድረግ ውላቸውን ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡