ቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካዩን ውል አራዘመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካዩ ሙሉዓለም መስፍንን ውል ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘሙን አስታውቋል።

በ2009 ክረምት ሲዳማ ቡናን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ሙሉዓለም በቡድኑ በመደበኛ ተሰላፊነት ያገለገለ ሲሆን ከብሔራዊ ቡድን መልስ ትላንት የሁለት ዓመት ውል ማራዘምያ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል።

ፈረሰኞቹ ሙሉዓለምን ጨምሮ እስካሁን የ7 ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያድሱ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡