ጋቶች ፓኖም ከግብፁ ክለብ ጋር ተለያየ

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አማካይ ጋቶች ፓኖም ከግብፁ ክለብ ኤል ጎውና ጋር መለያየቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

በ2010 ክረምት ላይ መቐለ 70 እንደርታን በመልቀቅ የግብፁን ክለብ የተቀላቀለው ጋቶች በተጠናቀቀው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ አመዛኝ ጨዋታዎች ላይ የመጀመርያ ተሰላፊ የነበረ ሲሆን ከክለቡ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ኤል ጎውና በትዊተር ገፁ ለተጫዋቹ ምስጋና እና መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ጋቶች በሩሲያው አንዚ ማካቻካላ እና መቐለ 70 እንደርታም ቆይታ አድርጓል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡