ፋሲል ከነማ ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅት የሜዳ ለውጥ ሊያደርግ ነው

ዐፄዎቹ ወደ ዳሬሰላም ለኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ከማምራታቸው ቀደም ብሎ የሚያከናውኑትን ዝግጅት አዲስ አበባ ላይ ሊያደርጉ ነው።

ባሳለፍነው እሁድ የመጀመርያውን ጨዋታ በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም አከናውነው በበዛብህ መለዮ ጎል 1-0 ማሸነፍ የቻሉት ፋሲሎች የመልሱን ጨዋታ የሚያከናውኑበት ቻማዚ ስታዲየም ሜዳ ሰው ሰራሽ በመሆኑ ለዝግጅት እንዲረዳቸው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ዝግጅት ለማድረግ ወስነዋል። በዚህም ሜዳውን ለመጠቀም ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅርበው መልስ እየጠበቁ እንደሆነ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት መጠነ ሰፊ የእድሳት ሥራ እየተከናወነለት የሚገኘው አበበ ቢቂላ ስታዲየም በቀጣይ የውድድር ዓመት ጨዋታ ለማድረግ ብቁ እንደሚሆን ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡