ኢትዮጵያ ቡና አራተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ቡና ሐብታሙ ታደሰን ዛሬ ማስፈረም ችሏል።

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ሐብታሙ ከቡሌ ሆራ ወልቂጤን ከተቀላቀለ በኋላ የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገ ሲሆን ቡድኑ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ወሳኝ አስተዋፅኦ አድርጓል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ናሽናል ሲሜንትን 7-2 ባሸነፉበት ጨዋታ ለብቻው ስድስት ጎሎች በማስቆጠርም የከፍተኛ ሊግ ሪከርድን መያዝ የቻለ ተጫዋች ነው።

ኢትዮጵያ ቡና እስካሁን ሁለት ከፕሪምየር ሊግ ሁለት ከከፍተኛ ሊግ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡