ዳዊት እስጢፋኖስ አዲስ አዳጊዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ

በፍጥነት በርካታ ተጫዋቾች እያስፈረሙ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ዳዊት እስጢፋኖስን ለማስፈረም ሲስማሙ በርካታ ትላልቅ ተጫዋቾች የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጨዋታ ህይወቱን የጀመረውና በመከላከያ ብዙዎች ዓይን ውስጥ የገባው ዳዊት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሊጉን ዋንጫ ካነሳ በኋላ በ2007 ቡድኑን ለቆ በድሬዳዋ ከተማ፣ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል ከነማ ተጫውቷል። ያለፈውን አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ደግሞ በመከላከያ ሲጫወት አሳልፏል። አማካዩ ወደ ሰበታ አምርቶ ከክለቡ የበላይ አካላት ንግግር ማድረጉ እና መስማማቱ ሲረጋገጥ በቅርቡ ፊርማውን ያኖራል ተብሎም ይጠበቃል።

ከዳዊት እስጢፋኖስ በተጨማሪ አንድ ግብ ጠባቂ፣ ሁለት አማካዮች እና አንድ አጥቂ ጨምሮ በርከት ያሉ በሊጉ ትልቅ ስም ያሌቸው ተጫዋቾችን የግላቸው ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡